ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ሲዳማ ቡና

ነገ ከሚደረጉት ሁለት የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል በትግራይ ስታድየም በሚደረገው የመቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል። 

ስድስት ጨዋታዎች አድርጎ 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው መቐለ 70 እንደርታ ነገ 09፡00 ላይ ምንም ሽንፈት ያልገጠመው ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ስሐል ሽረ ጋር ባደረጓቸው ጨዋታዎች ነጥብ የተጋሩት መቐለዎች ከአምናው ጋር ሲተያይ ደካማ አጀማመር ላይ ሲሆኑ ደረጃቸውን ለማሻሻልም ሁለቱ ተስተካካይ ጨዋታዎቻቸው ላይ ዕምነት ጥለዋል።  ከተጋጣሚያቸው በላይ አንድ ጨዋታ ያደረጉት ሲዳማዎች ግን ካለመሸነፋቸውም ባለፈ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው የእስካሀኑ የሊግ ጉዟቸው መልካም እንደሆነ ያሳያል። በሮድዋ ደርቢ አሸናፊ ከሆኑ በኋላም ወደ ጅማ ተጉዘው በተስተካካይ ጨዋታ ነጥብ መጋራታቸው ይያወሳል። በነገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ የማለት መቐለ ደግሞ ወደ ዘጠነኛነት የመጠጋት ዕድል ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የመቐለ 70 እንደርታው አሸናፊ ሃፍቱ እጁ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከነገው ጨዋታ ውጪ ሲሆን የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ መሳይ አያኖ መግባት እና አለመግባትም አለየለትም። ከዚህ ውጪ ሁለቱ ቡድኖች ከጉዳት እና ቅጣት ዜናዎች ነፃ ሆነው ሙሉ ስብስባቸውን በመጠቀም ለጨዋታው እንደሚደርሱ ይጠበቃል።   

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– ሁለቱ ክለቦች አምና በሊጉ እርስ በእርስ የተገናኙባቸው ጨዋታዎች በመሸናነፍ የተጠናቀቁ ነበሩ። በመጀመሪያው ዙር  ባለሜዳ የነበሩት መቐለዎች 1-0 ሲረቱ ሁለተኛው ዙር ደግሞ ሲዳማዎች ባስተናገዱት ጨዋታ 2-1 አሸንፈዋል።

– መቐለዎች ዘንድሮ ትግራይ ስታድየም ላይ ካደረጓቸው ሦስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥቦችን ሰብስበዋል። 

– ሲዳማ ቡና ከሀዋሳ ውጪ ያደረጋቸውን ሦስት ጨዋታዎች በሙሉ በአቻ ውጤት አጠናቋል። 

ዳኛ

– በሰባተኛው ሳምንት ሁለት የቢጫ ካርዶችን ያሳየበትን የመከላከያ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ የዳኘው ፌደራል ዳኛ ሐብታሙ መንግስቴ ይህን ጨዋታ ለመምራት ተመድቧል።

ግምታዊ አሰላለፍ

መቐለ 70 እንደርታ (4-2-3-1)

ፍሊፔ ኦቮኖ 

አሞስ አቼምፖንግ – አሌክስ ተሰማ – አሚኑ ነስሩ – አንተነህ ገብረክርስቶስ

ጋብርኤል አህመድ – ሚካኤል ደስታ 

አማኑኤል ገብረሚካኤል – ሐይደር ሸረፋ – ያሬድ ከበደ

ኦሰይ ማውሊ

ሲዳማ ቡና (4-3-3)

መሳይ አያኖ

ዮናታን ፍሰሃ – ፈቱዲን ጀማል – ሚሊዮን ሰለሞን – ግሩም አሰፋ

ዳዊት ተፈራ  – ግርማ በቀለ – ዮሴፍ ዮሃንስ 

ጫላ ተሺታ – ሐብታሙ ገዛኸኝ  –  አዲስ ግደይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *