የአሰልጣኞች አስተያየት | ” ውጤቱ የኛን እንቅስቃሴ አይገልፅም፤ ማሸነፍ ነበረብን”

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መቐለ ላይ ደደቢት ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ የደደቢቱ አሰልጣኝ ኤልያስ ኢብራሒም አስተያየታቸውን ሲሰጡ የአዳማ ከተማው ሲሳይ አብርሀምን አስተያየት ማካተት አልቻልንም። 

አልያስ ኢብራሒም – ደደቢት

“ጨዋታው እንዳያችሁት ነው። ቡድናችን ከጨዋታ ጨዋታ እየተስተካከለ ያለ ቡድን ነው። ከዕረፍት በፊት ጥሩ የግብ ዕድሎች ፈጥረን ግብም አስቆጥረናል። ከዕረፍት በፊት እንቅስቃሴያችን ጥሩ ነበር። ከዕረፍት በኋላም ብልጫ ነበረን፤ በአጠቃላይ ቡድናችን ወደ ጥሩ አቋም እየመጣ እንዳለ የታየበት ጨዋታ ነው።

” እንዳያችሁት በወጣቶች የተገነባ ቡድን ነው ያለን። ኳስን መሰረት አድርጎ የሚጫወት ቡድንም ነው። ለቀጣይ የኢትዮጽያ እግር ኳስ ትንሳኤ ማበሰር የሚችሉ ተጫዋቾች የያዘ ነው። የተሻለ ነገር ባገኙ ቁጥር የተሻለ መስጠት እንደሚችሉ አይተናል። ቡድኑ የተሻለ ነገር ካገኝም ባጠቃለይ ቡድኑ የመነሳሳት አቅሙ የተሻለ ነው። እንዳረግነው እንቅስቃሴ ጥሩ ነገር ይመጣል ብለን እንጠብቃለን።

ስለ ዛሬው ውጤት

እንደ ዛሬ እንቅስቃሴ ውጤቱ የኛን አቅም አይገልፅም፤ ማሸነፍ ነበረብን። ከዚ ጨዋታ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዘን መውጣት ነበረብን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *