አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ በይፋዊ የሽኝት መርሐ-ግብር ከስሑል ሽረ ጋር ተለያዩ

ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ስሑል ሽረን በአሰልጣኝነት ያልመሩት እና ከክለቡ ጋር እንደሚለያዩ ሲጠበቁ የነበሩት ዳንኤል ጸሐዬ እና ረዳታቸው ዛሬ በተደረገ የሽኝት መርሐ ግብር መለያየታቸው እርግጥ ሆኗል።

የቀድሞው የጉና ንግድ የመስመር ተጫዋች እንዲሁም የደደቢት እና ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ከ2009 ጀምሮ ሽረን ሲያሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ቡድኑን ወደ ሊጉ ቢያሳድጉም በዘንድሮው ዓመት ማሰልጠን እስካቆሙበት ጊዜ ድረስ ድል ማስመዝገብ ተስኗቸው ቆይቷል። ክለቡ ከድሬዳዋ ከተማ እና ደደቢት ጋር ባደረጉት ጨዋታ  ላይ አለመምራታቸውን ተከትሎ ስንብታቸው ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ዛሬ አመሻሹ ላይም የሽኝት ፕሮግራም ተደርጎላቸዋል።

በዛሬው መርሐ-ግብር ከአሰልጣኙ ባሻገር ምክትል አሰልጣኝ በረከት ገብረመድኅን እንዲሁም የቡድን መሪው ኤፍሪም ሓዱሽም ከቡድኑ ጋር መለያየታቸው ይፋ ሆኗል። የክለቡ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ምሽት የእራት ግብዣ የተደረገ ሲሆን ሶስቱም ለሰሩት ስራ እውቅና እና ምስክር ወረቀት እንዲሁም የአንገት ሀብል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *