​የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-1 ባህር ዳር ከተማ

​ከ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል ጅማ አባ ጅፋር ከባህር ዳር ከተማ 1-1 ከተለያዩ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ቀጣዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል።

“ትልቁ ድክመታችን አጨራረስ ነበር” የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር ም/አሰልጣኝ

ስለጨዋታው

“በጨዋታው ጥሩ ተንቀሳቅሰናል። ከእረፍት በፊት ያገኘናቸውን የግብ ማግባት  አጋጣሚዎች አለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል። በዛሬው ጨዋታ ትልቁ ድክመታችን አጨራረስ ነበር። ወደ ግብ እየደረስን አናገባም ነበር። ለሚቀጥለው ጨዋታ ይህን ችግር ለመቅረፍ ትኩረት አሰጥተን እንሰራለን።”

ስለተጫዋቾች ቅያሪ

“በኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ምክንያት ብዙ ተደራራቢ የሊግ ጨዋታዎች ከፊት ይጠብቁናል። ለዛ በማሰብ ጉልበት ለመቆጠብ ነው ቅያሪዎችን ያደረግነው።”  

“በሁለተኛው አጋማሽ  በሜዳችን የምንጫወት እስኪመስለን ጨዋታውን ተመቆጣጥረን ወጥተናል”  አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው – ባህር ዳር ከተማ

ስለጨዋታው

“በመጀመሪያው አጋማሽ የፀሀዩ ጥንካሬ ተቀላቅሎበት በተጋጣሚያችን ተበልጠን ነበር። ወደፊት ለመሄድ በምናደርገው ጥረት የመስመር አጥቂዎቻችን ወደ ኃላ በመሳባቸው ጃኮ ብቻውን ተቸግሮ ነበር። ውጤታማ አልነበንም ፤ በሁለተኛው አጋማሽ  በሜዳችን የምንጫወት እስኪመስለን ጨዋታውን ተመቆጣጥረን ወጥተናል፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *