ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ተለያየ

ካለፉት ዓመታት አንፃር በውድድር ዘመኑ የተቀዛቀዘ ውጤት እያስመዘገበ ያለው ሀላባ ከተማ ከአሰልጣኙ ሚሊዮን አካሉ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ከሚባሉ ክለቦች መካከል አንዱ ነው ሀላባ ከተማ ያለፉትን አምስት ዓመታት ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ጫፍ እየደረሰ ሲመለስ በተደጋጋሚ ተመልክተናል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ደግሞ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲወዳደር ዝቅተኛ ውጤትን እያስመዘገ ይገኛል። በተለይ በስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በወላይታ ሶዶ 4-0 ከተረታ በኃላ ከዋና አሰልጣኙ ሚሊዮን አካሉ ጋር ለመለያየት ከውሳኔ ደርሷል።

በ1990ዎቹ አጋማሽ ስኬታማ የተጫዋችነት ዘመንን በሀዋሳ ከተማ ያሳለፈው አሰልጣኝ ሚሊዮን አካሉ በአንድ አጋጣሚ ወደ ሻሸመኔ አምርቶ ከሰራበት የአሰልጣኝነት ህይወቱ በስተቀር ለረጅም ዓመታት ሀላባ ከተማን በማሰልጠን ነው የሚታወቀው። በ2009 ዳግም ወደ ክለቡ የተመለሰው አሰልጣኙ ያለፉትን ሁለት ከግማሽ ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ ነው የተለያየው።

ሀላባ ዋና አሰልጣኝ እስኪቀጥር ድረስ በምክትሉ መኮንን ገላነህ በጊዜያዊነት እየተመራ የሚቀጥል ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *