ስሑል ሽረዎች አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ ከአንድ ተጫዋች ጋር ተለያይተዋል

ስሑል ሽረዎች ከሄኖክ ብርሃኑ ጋር በስምምነት ሲለያዩ አሳሪ አልመሃዲን አስፈርመዋል።

ባለፈው ዓመት ወልዋሎ ከመከላከያ በነበረው ጨዋታ አርቢቴር እያሱ ፈንቴ ላይ በደረሰው ድብደባ ተሳታፊ ነበር በሚል ላለፉት ወራት ቅጣት ላይ የቆየው አሳሪ አልመሃ ስሑል ሽረን መቀላቀሉ እርግጥ ሆኗል። በ2009 የውድድር ዓመት አጋማሽ ድሬዳዋ ከተማን ለቆ ወልዋሎ በመቀላቀል ቡድኑን በተለያዩ የጨዋታ ሚናዎች በቋሚነት ሲያገለግል የነበረው በሁለተኛው ዙር ለሽረ መጫወት የሚጀምር ሲሆን በበርካታ አማካይ ተጫዋቾች መልቀቅ ምክንያት የተፈጠረው ክፍተት ይሞላል ተብሎም ይጠበቃል።

ባለፈው ሳምንት ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት የተለያዩት ስሑል ሽረዎች አሁን ደሞ ባለፈው ዓመት ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የቡድኑ አባል ከነበረው የአማካይ ክፍል ተጫዋች ሄኖክ ብርሃኑ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።

በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኙት ሽረዎች ከተጫዋቾች በተጨማሪ ከዋና አሰልጣኙ ዳንኤል ፀሐዬ፣ ምክትሉ በረከት ገብረመድህን እና ቡድኑን ለበርካታ ዓመታት በቡድን መሪነት ያገለገለው ኤፍሬም መለያየታቸውም ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *