የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-0 ደደቢት


በ6ኛ ሳምንት ቀሪ ተስተከይ መርሐ ግብር ጅማ አባጅፋር ደደቢትን 1-0 ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል።

የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር

ስለ ጨዋታው

ወደ ሜዳ የገባነው ደጋፊዎችን ለመካስ ነበር።
ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ፖሊስ የደረሰብንን ሽንፈት ለማካካስ አስበን ነበር ወደ ሜዳ የገባነው። ከእረፍት በፊት የፈጠርናቸውን እድሎች አለመጠቀማችን ተዳምሮ ተጫዋቾቹ ላይ ጭንቀት ውስጥ ከቷቸው ነበር። ሆኖም በዛሬው ጨዋታ የምንፈልገው ውጤት አግኝተናል።

መሐል ሜዳ ላይ ስለተወሰደባቸው ብልጫ

መስዑድ ከሌላው ግዜ አንፃር ተዳክሞ ነበር። በዚህም በተወሰነ መልኩ መሀል ላይ ተበልጠናል። መሀል ላይ ከሱ ጋር የሚጫወቱት እና ተቀያሪም ላይ ያሉን ተጫዋቾች የመከላከል ባህሪ ያላቸው ስለሆኑ መስዑድን ሜዳ ላይ አቆይተነዋል።

በቀጣይ…

ከዚህ በኃላ ቀሪ ያሉንን ቀሪ ጨዋታዎች አሸንፈን ከ20 በላይ ነጥቦች በመያዝ የመጀመሪያውን የውድድር ጊዜ ለመጨረስ እንሞክራለን።

ዳንኤል ፀሐዬ – ደደቢት

ወደዚህ የመጣነው ቢያንስ አቻ ውጤት ለማግኘት ነበር። ከተደጋጋሚ ሽንፈት ለማገገምና የመጀመሪያውን ዙር በጥሩ መንፈስ ለመጨረስ የዛሬው ጨዋታ ለኛ ወሳኝ ነበር። ነገር ግን አልተሳካም።

ጨዋታውን ጥሩ ተቆጣጥረን ተጫውተን ነበር። ተጨዋቾቻችን ወጣቶች ናቸው። ረጃጅም ኳሶች ላይ ስንከላከል ትንሽ ቅንጅት አልነበረንም። የገባብንም በቆመ ኳስ ከትኩረት ማነስ የተቆጠረብን ነበር። እነሱ በፕሪምየር ሊጉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ስላሏቸው ልምዳቸው ጠቅሟቸዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *