ጅማ አባጅፋር የስንብት ውሳኔ አሳለፈ

ጅማ አባጅፋር ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ስራ አስኪያጁን ማሰናበቱን የክለቡ ፕሬዝዳንት አጃይብ አባመጫ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ትላንት ደደቢትን 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ወደ ድል የተመለሰው አባጅፋር ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ለቡድኑ ደካማ የውድድር ዘመን አስተዋጽኦ ነበራቸው ያላቸው ላይ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን እና ውሳኔ ማስተላለፋቸውን የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አጃይብ አባመጫ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የቡድኑ ስራ አስኪያጅ አቶ እስከዳር ዳምጠው ከስራ እንዲሰናበቱ እንደተወሰነ ገልፀው ከአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ፣ ምክትሉ የሱፋ ዓሊ፣ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ መሐመድ ጀማል እና የቡድን መሪው ጁሐድ ከድር ጋር የቡድኑ ውጤት በሚሻሻልበት ሁኔታ ዙርያ ውይይት እንዳደረጉ ገልፀዋል።

አቶ አጃይብ በተጨማሪም አምና ቅጣት ተጥሎበት ቅጣቱ ያልተነሳለት እና ዘንድሮ በአንድም ጨዋታ ጅማን መምራት ያልቻሉት ዋና አሰልጣኙ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በቀጣዩ ወር ሙሉ ለሙሉ ቅጣታቸውን ስለሚጨርሱ ከቡድኑ ጋር እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ እንደሚቀጥሉ የተረጋገጠ  የዲሲፕሊን ችግር ላለባቸው ተጫዋቾችን በቀጣዩ ጊዜ የማስጠንቀቂያ እና የስንብት ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል።

የአምናው ቻምፒዮን ጅማ አባጅፋር ዘንድሮ ከሜዳ ላይ ውጤት በተጨማሪ በአስተዳደራዊ ድክመት ምክንያት የጉዞ መጉላላት፣ የደሞ ክፍያ መዘግየት እና የመሳሰሉት ሲስተዋሉ ቆይተዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *