የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-0 መከላከያ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፋር ከመከላከያ ካደረጉት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን ብለዋል።

” ከጨዋታው የምንፈልገውን አሳክተን ወጥተናል” የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር

” የዛሬው ጨዋታ ሁለታችንም ኳስን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረናል። ግቧን በመጀመርዎቹ ደቂዎች በማስቆጠራችን ምክንያት ከዛ በኋላ ያሉትን ደቂቃዎች ግቧን ለማስጠበቅ ነው የተጫወትነው። ምክንያቱም ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች ስላሉን እና እየተጫወትን ያለነው በየአራት ቀን ልዩነት በመሆኑ ትኩረታችን ውጤት ማስጠበቁ ላይ ነበር።

ከእረፍት መልስ የተሻለ ቢንቀሳቀሱም እኛ ከጨዋታው የምንፈልገውን ሦስት ነጥቦች አሳክተን ወጥተናል።

“ከዚህ የተሻለ ይገባን ነበር ” ሥዩም ከበደ – መከላከያ

ስለ ጨዋታው

ወደዚህ ስንመጣ የዙሩ የመጨረሻ ጨዋታችን እንደመሆኑ ከፍተኛውን ነጥብ አሳክተን ለመመለስ ነበር ፍላጎታችን፤ እንደመሰብነው አልተሳካም። የመከላከል አደረጃጀታችን ላየ ችግር አለ። ያለፉትን ጨዋታዎች መሻሻል ብናሳይም አሁንም ውጤት እያጣን ያለው በዚሁ ችግር ነው። በአጠቃላይ ግን ጨዋታው ጥሩ ነበር። ጅማዎች በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ፤ እኛ ደግሞ በሁለተኛው የተሻልን ነበርን። ዞሮ ዞሮ ከዚህ የተሻለ ውጤት ፤ ቢያንስ አቻ ይገባን ነበር ብዬ ነው የማስበው።

ስለ መከላከል እና አንደኛው ዙር

ቡድናችን ጥሩ ሊጫወት የሚችል ቡድን ነው። ነገር ግን ከአዳማው ጨዋታ በኋላ እንቅስቃሴያችን ተፅዕኖ ውስጥ ገብቷል። የመከላከል አጨዋወታችንን ማስተካከል አለብን። መከላከል ስል ተከላካዮቹን በቻ ሳይሆን አጠቃላይ የቡድኑን የመከለከል ባህርይ ማስተካከል አለብን።

እንደ እቅድ በያዝነው መንገደ ጥሩ እየሄድን ነበር። ጥሩ የዝግጅት ጊዜ አሳልፈን የጥሎ ማለፍ እና አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫዎችን በማንሳት ነበር ዓመቱን የጀመርነው። በአፍሪካ ውድድር ላይም ተሳትፈናል። ሆኖም ከጊዜ በኋላ ውጤታችን ሊወርድ ችሏል። ሁለተኛው የውውድር ዘመን አጋማሽን በተከታታይ በሜዳችን በምናደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ስለምንጀምር እነሱን አሸንፈን ለማንሰራራት ነው የምናስበው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *