ደደቢት በርካታ ተጫዋቾችን አሰናበተ

በዚህ ዓመት አካሄዱን ቀይሮ ለመወዳደር ከወሰነ በኋላ በዝቅተኛ ሊጎች የሚጫወቱ እና ከታዳጊ ቡድን ካሳደጋቸው በርካታ ተጫዋቾች ጋር ዓመቱን የጀመረው ደደቢት አስራ ሁለት ተጫዋቾችን አሰናብቷል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ክለቡ ያሰናበታቸው ተጫዋቾች ምስጋናው መኮንን፣ ሙሉጌታ ብርሃነ፣ ስንታየሁ ታምራት፣ ተመስገን በጅሮንድ፣ ፋሲል አበባየሁ፣ ያሬድ መሐመድ፣ ሙሉቀን ተስፋዬ፣ ማቲያስ ሰይፉ፣ በሱፍቃድ ደበሳው፣ ጥዑመልሳን ገብረሚካኤል አክዌር ቻሞ እና ዓወት ናቸው።

ደደቢት ባሳለፍነው ሳምንት ኑሁ ፉሴይኒ፣ ሮበን ኦባማ እና አንቶንዮ አባውላ ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን በሀገር ውስጥ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾች በለቀቁት ምትክ እንደሚፈርሙ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *