የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የተስተካከለ መርሐ ግብር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ የውድድር ዘመን አጋማሽ በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚጀምር አስቀድሞ የወጣው መርሐ ግብር ቢያሳይም መጋቢት 1 ሊደረጉ በነበሩ ጨዋታዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።

በዚህም መሠረት መጋቢት 1 ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች በሙሉ ወደ በአንድ ሳምንት ተራዝመው የሚከናወኑ ሲሆን መጋቢት 8 ሊደረጉ የነበሩት ጨዋታዎች ግን በተያዘላቸው ጊዜ መሠረት ይከናወናሉ።

የ16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር

ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2011
ወልዋሎ ከ ሀዋሳ ከተማ (9:00 መቐለ)

እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2011
ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (9:00 ባህር ዳር)
ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ (9:00 ሶዶ)
ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (9:00 ድሬዳዋ)
መከላከያ ከ ደቡብ ፖሊስ (10:00 አዲስ አበባ)
ጅማ አባ ጅፋር ከ አዳማ ከተማ (9:00 ጅማ)
ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና (9:00 ጎንደር)
ደደቢት ከ መቐለ 70 እንደርታ (9:00 መቐለ)

በተያያዘ ዜና መጋቢት 7 በኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ መካከል ሊከናወን የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ግንቦት 1 መሸጋገሩ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *