መከላከያ የምክትል አሰልጣኝ እና ቡድን መሪ ለውጥ አደረገ

ወጥ ባልሆነ አቋም የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ አጋማሽ ያጠናቀቀው መከላከያ የ2011 የአንደኛው ዙር የውድደር አፈፃፀም አስመልክቶ የክለቡ የቦርድ አመራሮች ባደረጉት ግምገማ የምክትል አሰልጣኝ እና የቡድን መሪ ለውጥ አድርገዋል።

ያለፉትን ስድስት ወራት የአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ረዳት በመሆን ሲያገለግል የነበረው አሰልጣኝ ኑረዲን አደምን በማንሳት ዓምና የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ያገለገሉት እና በአሁኑ ወቅት የሴቶች ዋና አሰልጣኝ በመሆን እየሰሩ የሚገኙት አሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬን ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል። አሰልጣኝ ኑረዲን ደግሞ ከ20 ዓመት በታች ቡድንን ዋና አሰልጣኝ በመሆን እንዲያገለግል ተደርጓል።

ለረጅም ዓመት የቡድን መሪ በመሆን ያገለገሉት ሙሉ ባራኪ ተነስተው ዓለሙ ዘነበ ተተክተዋል። የሴቶች ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ ደግሞ የቀድሞው የዋናው ቡድን አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳን ተሹመዋል።

መከላከያ በውድደር ዘመኑ በአስራ አምስት ጨዋታ 17 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *