ስሑል ሽረ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቀ

ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በዝውውሩ በሰፊው እየተሳተፉ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች ጋናዊው ጋይሳ ቢስማርክ እና አይቮሪኮስታዊው ሳሊፉ ፎፋናን አስፈርመዋል።

በጥር የዝውውር መስኮት በሰፊው እየተሳተፉ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች በመጀመርያው ዙር የታየባቸው የግብ ማግባት ችግር ለመፍታት የጀመሩት ስራ ሁለት የማጥቃት ባህሪ ያላቸው ተጫዋቾች በማስፈረም አስቀጥለዋል። ባለፈው ዓመት ከመቐለ 70 እንደርታ ጥሩ ዓመት ያሳለፈው ጋናዊ ጋይሳ አፓንግ ቢስማርክ እና ኮትዲቫራዊው ሳሊፉ ፎፎናም አስፈርመዋል።

ባሳለፍነው ዓመት የጋናው ክለብ መዳማ ለቆ ለመቐለ 70 እንደርታን በመፈረም ከቡድኑ ጋር የተሳካ ዓመት ያሰለፈው ይህ ጋናዊ አጥቂ ከስድስት ወራት ቆይታ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለስ ይሆናል። በፊት አጥቂነት፣ በአጥቂ አማካይ መሰለፍ የሚችለው እና ከረጅም ርቀት በሚያስቆጥራቸው ግቦች የሚታወቀው ቢስማርክ ከቀናት በኃላ ወደ ስሑል ሽረ የሚቀላቀል ይሆናል።

ሌላው በተሰጠው የሙከራ ዕድል ክለቡን አሳምኖ ፈርማውን ያኖረው አይቮሪኮስታዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሳሊፉ ፎፋና ነው። እንደ ቢስማርክ ሁሉ በአጥቂነት እና በመስመር መጫወት የሚችለው ይህ የቀድሞ አል-ሃላሙሃራ፣ አፍሪካ ስፖርትስ እና ማንጋ ስፖርት አጥቂ በመጀመርያው ዙር በማጥቃት ባህሪ ተጫዋች እጦት ለተቸገሩት ስሑል ሽረዎች ጥሩ ፊርማ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *