የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያ ቡና እና ሸረፋ ዴሌቾ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ኢትዮጵያ ቡና በዳኞች ኮሚቴ የስም ማጥፋት ድርጊት ፈፅሟል በሚል፤ ኮሚሽነር ሸረፋ ዴሌቾን ደግሞ በመቐለ እና ፋሲል ጨዋታ ዙርያ ቅጣት እንዳስተላለፈ በይፋዊ ድረ-ገፁ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ታህሳስ 15 ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በላከው የቅሬታ ደብዳቤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴን አባላት እምነት የሚጣልባቸው እንዳልሆነ በመግለፅ በአባላቶቹ እምነት ሊያድርባቸው እንዳልቻለ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ክለቡ የላከውን የቅሬታ ደብዳቤ ተንተርሶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከስድስት ቀናት በኋላ (ታህሳስ 21) ቅሬታቸውን በመረጃ አስደግፈው እንዲያስረዱ ለቡናዎች ጥያቄ አዘል ምላሽ ቢልክም ክለቡ ምላሽ ለመስጠት እንዳልቻለ ፌደሬሽኑ ያወጣው የቅጣት ዝርዝር ላይ አያይዞ ገልጿል። ይሁንና ጥር 30 የዲሲፕሊን ኮሚቴ ክለቡ በተሰጠው ጊዜ ጉዳዩን በመረጃ ሊያብራራ አልቻለም በሚል ቅጣት ለመጣል ክለቡን የመከላከያ ምላሽ ጠይቋል።

የዲሲፕሊን ኮሚቴን ጥያቄ ተቀብለው የካቲት 7 ምላሽ የሰጡት ኢትዮጵያ ቡናዎች “መረጃ አምጡ ልንባል አይገባም” የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ለፌደሬሽኑ በመላክ ምላሽ ሰጥተዋል። ይህንን ጉዳይ ሲመረምር የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ክለቡ የቡሄራዊ ዳኞች ኮሚቴን እና ሰብሳቢ ላይ የስም ማጥፋት ድርጊት ፈፅሟል በማለት የ50 ሺ ብር ቅጣት አስተላልፏል።


በተያያዘ የቅጣት ዜና ኮሚቴው ጥር 30 መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ ኮሚሽነር የነበሩት ሸረፋ ዴሌቾ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል። በውሳኔውም ኮሚሽነሩ ጨዋታው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ3 ወራት ከውድድሮች እንዲርቁ (1 ወሩ በመጠናቀቁ ቀጣዮቹ 2 ወራት ነው የሚቀጡት) ወስኗል።

የኮሚሽነር ሸረፋ ዴሌቾ ቅጣት ማብራሪያ ይህንን ይመስላል:-




© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *