የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አዲስ አበባ ይገኛሉ

ለሁለት ሀገራት ብሔራዊ ቡድን የተጫወቱት እና በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚነሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆኑት የወቅቱ የኤርትራ ብሔራዊ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ነጋሽ ተክሊት በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ይገኛል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ ተጫዋች በ1970ዎቹ በኢትዮጵያ እግርኳስ ከሚጠቀሱ ምርጥ ተጫዋቾች አንዱ የነበሩ ሲሆን በኤርትራ ጫማ ክለብ በነበራቸው ቆይታ በ1979 የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆነው አጠናቀዋል። በ1980 ኢትዮጵያ ራሷ አስተናግዳ ቻምፒዮን በሆነችበት የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ላይ በፍፃሜው መለያ ምት ካስቆጠሩ ተጫዋቾች አንዱ ነበሩ። የኋላም ለኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት አገልግለዋል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

የወቅቱ የኤርትራ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ለተወሰኑ ቀናት በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በዋናነት በአስመራ የሚካሄደውን “የሠላም እና ወዳጅነት ከ20 ዓመት በታች ውድድር ” በተመለከተ ባሉ ጉዳዮች ዙርያ ለመነጋገር እንደሆነ የሰማን ሲሆን ውድድሩም አስቀድሞ በወጣለት መርሐግብር መሠረት እንደሚካሄድና ውድድሩ እንደማይራዘም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ዛሬ ምሻውንም በአዲስ አበባ ስቴዲየም በመገኘት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ከማሊ ጋር የሚያደርገውን የማጣሪያ ጨዋታም እንደሚከታተሉ ለማወቅ ችለናል።

የነጋሽ ተክሊት ሰፊ የእግርኳስ ህይወትን የተመለከተ ከሶከር ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሰፊ ቆይታ ወደፊት ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ መጠቆም እንፈልጋለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *