ኢትዮጵያ ቡና ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው

በ17ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ከደደቢት ጋር ሊያካሄደው የነበረው ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።
ኢትዮጵያ ቡና የፊታችን እሁድ 10:00 ከደደቢት ጋር ሊያካሂደው የነበረው መርሐግብር አራት ተጫዋቾቹ አማኑኤል ዮሐንስ፣ አቡበከር ናስር፣ ሐሰን ሻባኒ እና ክሪዚስቶም ንታምቢ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ምክንያት ከቡድኑ ውጭ በመሆናቸው ወደ ሌላ ቀን ጨዋታው እንዲራዘምለት በጠየቀው መሰረት ፌዴሬሽኑ ጨዋታው መራዘሙን ከሰዓታት በፊት በይፋ ማሳወቁ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር ነገ ረፍድ 04:00 በያያ ቪሌጅ ሜዳ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል። አል ሜሪክ ባሳለፍነው ረቡዕ በወዳጅነት ጨዋታ ከፋሲል ከነማ ጋር ያለ ጎል በአቻ ውጤት መለያየቱ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *