የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ልምምድ አቁመዋል

የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ክለቡ ያለፉትን ሶስት ወራት ደመወዝ ባለመክፈሉ ዛሬ ልምምድ አቁመዋል፡፡

ከጅማ አባጅፋር ጋር ነጥብ ተጋርቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈትን በማስተናገድ ሁለተኛውን ዙር የጀመረው አዳማ ከተማ ተጫዋቾቹ ያለፉትን ሶስት ወራት የደመወዝ ክፍያን ባለማግኘታቸው ዛሬ መደበኛ ልምምዳቸውን ሳይሰሩ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ሶከር ኢትዮጵያ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አንበሴን ያነጋገረች ሲሆን ” እስከ ሀሙስ ክፍያው ሙሉ በሙሉ ለመክፈል ወስነናል፤ ይህንንም እንፈፅማለን” ሲሉ ገልፀዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *