የሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን የመጀመርያ ምዕራፍ ዝግጅቱን አጠናቀቀ 

በአሰልጣኝ ሠላም ዘራይ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ምዕራፍ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ አራት ተጫዋቾችን ቅነሳ አደረገ።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 29 ተጫዋቾችን በመያዝ በአዲስ አበባ ስታዲየም በቀን ሁለቴ ልምምዱን በጥሩ ሁኔታ እየሰራ የሚገኘው የሴቶች ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን የዝግጅቱን የመጀመርያ ምዕራፍ ልምምድ ትናንት ማምሻውን ከወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ በአዲስ አበባ ስቴዲየም በመስራት አጠናቋል።

በመጀመርያ ምርጫ ጥሪ ከተደረገላቸው 29 ተጫዋቾች መካከል አራት ተጫዋቾች በዛሬው ዕለት ተቀንሰዋል። ምህረት ተሰማ (ግብጠባቂ) ፣ ትዕግስት ኃይሌ (ተከላካይ) ፣ ትዕግስት ያደታ (አማካይ) እና ዮርዳኖስ ምዑዝ (አጥቂ) የተቀነሱት ተጫዋቾች ናቸው። አሁን 25 ተጫዋች የቀሩ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ዮጋንዳ አቻውን እስኪገጥም ድረስ ተጫዋቾቹ ከቡድኑ ጋር አብረው እንደሚቆዩ ተረጋግጧል።

አሰልጣኝ ሠላም ዘራይ በሁለተኛ ምዕራፍ ዝግጅቷ የአቋም መፈተጫ ጨዋታ ከመሰል ሀገራት ጋር ለማድረግ ያደረገችው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም ነገ 10:00 በአዲስ አበባ ስቴዲየም ከወንዶች ታዳጊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዛለች።

የሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ መጋቢት 25 የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚያደርጉት የኦሊምፒክ ሴቶች ቡድን የመልስ ጨዋታቸውን ከሦስት ቀን በኃላ በዩጋንዳ ካምፓላ የሚያደርጉ ይሆናል። እንስቶቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ ድል የሚቀናቸው ከሆነም ቀጣይ ተጋጣሚያቸው ካሜሩን እንደምትሆን ካፍ አሳውቋል።

የመጨረሻ 25 ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ማርታ በቀለ (መከላከያ)፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት) እና አባይነሽ ኤርቄሉ (ሀዋሳ ከተማ)


ተከላካዮች

መስከረም ካንኮ (አዳማ ከተማ)፣ መሠሉ አበራ (መከላከያ)፣ ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ አሳቤ ሙሶ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሠ (ኢትዮ ንግድ ባንክ)፣ እፀገነት ብዙነህ (አዳማ ከተማ)፣ ናርዶስ ዘውዴ (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት ፀጋዬ (አዳማ ከተማ)


አማካዮች

ሕይወት ዳንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ)፣ ብርሃን ኃይለሥላሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) እና አረጋሽ ከልሳ (መከላከያ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (አዳማ ከተማ)፣ ሴናፍ ዋኩማ (አዳማ ከተማ)፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ)፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሔለን እሸቱ (መከላከያ)፣ ምስር ኢብራሂም (ጥረት ኮርፖሬት)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply