የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ለዳኞች የአካል ብቃት ፈተና እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠናን መስጠት ጀመረ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዳኞች ኮሚቴ አሁን ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ እና አንደኛ ሊግ ለሚገኙ ዳኞች መስጠትን ዛሬ ጀመረ፡፡

በሁለተኛው ዙር ዳኞች በአካል እና በአዕምሮ ጎልብተው ውድድሮችን በወጥነት መምራት እንዲችሉ የፌዴሬሽኑ የዳኞች ኮሚቴ በቅርቡ ለበርካታ የፕሪምየር ሊግ ዳኞች እና የኮሚሽነርነት ሙያ ውስጥ ላሉ የአካል ብቃት እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና የሰጠ ሲሆን አሁን ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ እና አንደኛ ሊጉ ላሉ ዳኞች የአካል ብቃት ፈተናን መስጠት ጀምሯል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በከፍተኛ ሊጉ ላሉ በርካታ ዳኞች የአካል ብቃት ፈተና ማከናወን የተጀመረ ሲሆን ነገ ደግሞ የአንደኛ ሊግ ዳኞች ይህን የአካል ብቃት ምዘናውን የሚወስዱ ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬን ጨምሮ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ እና የኮሚቴው አባላት በተገኙበት ፈተናው መሰጠት የተጀመረ ሲሆን በእለቱ የተሳተፉት አብዛኛዎቹ ዳኞች የአካል ብቃት ችግሮችን አስተውለናል።

ከብቃት ምዘናው መጠናቀቅ በኋላ ከነገ ጀምሮ በክፍል ውስጥ አዳዲስ በተሻሻሉ ህጎች ላይ ስልጠና እና የምክክር መድረክ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *