ሪፖርት | አዳማ ከነማ በሜዳው በግብ ተንበሽብሾ ስሑል ሽረን አሸንፏል

በ18ኛዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ላይ በ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስስሑል ሽረን ያስተናገደው አዳማ ከተማ 4-1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በጨዋታው መጀመሪያ ላይ በአዳማ ደጋፊዎች የግማሽ ዓመቱ ኮኮብ ተጫዋቾች ሸልመዋል። በዚህም አድየ የኔ የቴሌግራም ቻናል ላይ በተሰበሰበ ድምፅ ከንዓን ማርክነህ የግማሽ ዓመቱ ኮኮብ ተጫዋቾች ተብሎ ተመርጧል። ሌላኛዉ ተሸላሚ ኢስማኤል ሳንጋሪ ደግሞ በአዲስ አድባራት የፌስቡክ ገፅ አዘጋጆች እንዲሁ የግማሽ ዓመቱ ኮኮብ ሆኗል።

አዳማ ከተማዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ 1- 0 ተሸንፎ ከመጣዉ ስብስብ በርካታ ለዉጦች አድርገዉ ነበር ወደሜዳ የገቡት ጃኮ ፔንዜን በሮበረት ኡዳንካራ ፣ ዐመለ ሚልኪያስን በብሩክ ቃልቦሬ ፣ እንዲሁም በዳዋ ሆቴሳ  ምትክ ከንዓን ማርክነህን በቅጣት ምክንያት ባልተሰለፈዉ አምበሉ ምኞት ደበበ ቦታ ሱለይማን ሰሚድ እና በሱራፌል ዳንኤል ደግሞ ሱለይማን መሀመድን ተክተዉ ነበር ወደሜዳ የገቡት። ስሑል ሽረ በአንፃሩ ባህርዳር ከነማን በሜዳዉ 1-0 አሸንፎ ከመጣው ስብስብ ሀብታሙ ሸዋለምን በሙሉዓለም ረጋሳ በመተካት ጨዋታውን ጀምረዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ አጥቅተዉ የተጫወቱት አዳማ ከተማዎች በተደጋጋሚ ከርቀት ወደ ግብ ሲሞክሩ ይስተዋል ነበር። በ7ኛው ደቂቃ ከነዓን ማርክነህ ከሳጥን ዉጪ ወደ ግብ እክርሮ የመታዉን እንዲሁም በተመሳሳይ አዲስ ህንፃ ከሳጥን ዉጪ 9ኛ ደቂቃ ላይ ያደረገውን ሙከራ ግብ ጠባቂ አድኖበታል። በተደጋጋሚ የሽረ ግብ ክልል እየደረሱ ያነበሩት አዳማ ከነማዎች 13ኛ ደቂቃ ላይ ከበረከት ደስታ የተሻማዉን የቅጣት ምት ግብ ጠባቂ ይዞ ሲያመልጠው አዲስ ህንፃ በመድርስ ግብ አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹን መሪ ማድረግ ችሏል።

በእንቅስቃሴ ረገድ ቀዝቃዛ በነበረው ጨዋታ የሽረን የተከላካይ መስመር ሰብሮ ከመግባት አንፃር የከበዳቸው አዳማዎች በተደጋጋሚ ከርቀት አክርረዉ የሚመቷቸዉ ኳሶች በርካታ ነበሩ። 19ኛ ደቂቃ ላይ ከንዓን ማርክነህ ከሳጥን ዉጭ አክርሮ የመታዉ ኳስም በዚህ ውስጥ የሚካተት ነበር ። ሽረዎች በመስመር የሚመሰርቱትን ኳስ የአዳማ የመስመር ተጫዋቾች በማጨናገፋ ተጭነዉ ሲጫወቱ ይስታዋል ነበር። 20ኛ ደቂቃ ላይ ሱለይማን ሰሚድ አክርሮ የመታዉን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲያወጣበት ባለሜዳዎቹ በመስመር የተሻለ ተጭነዉ በመጫወት በድጋሜ 23ኛ ላይ በግራ መስመር ከነዓን ማርክነህ ያሸገረለትን ኳስ ሱለይማን መሀመድ  ከግብ ጠባቂ ጋር ተገናኝቶ አምክኗል።

25ኛ ደቂቃ ላይ በመስመር ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ በረከት ደስታ ሳጥን ዉስጥ ያገኝዉን ኳስ ወደ ግብ ሲመታ በግብ ጠባቂዉ ተጨርፎ ከጀርባው ሲነጥር ሱለይማን ሰሚድ ብቻዉን ከግብ ጋር ተገናኝቶ በማስቆጠር የግብ ልዩነቱን ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችሏል። ከዚህ ቀደም ከሚሰጠዉ ሚና በተለየ ፊት መስመር ላይ በመጨረሻ አጥቂነት ሚና ይዞ የገባዉ እና የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረገዉ ከንዓን ማርክነህ 44ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር ሁለት ተጫዋቾችን አልፎ ወደ ቀኝ የሳጥኑ ጠርዝ ያሻገረለትን ኳስ ሱራፌል ዳንኤል ያመከነዉ በመጀመሪያው አጋማሽ የሚጠቀስ ሌላኘው የአዳማዎች ሙከራ ነበር። 

በስሑል ሽረ በኩል ጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ ረጃጅም ኳሶችን ለመጠቀም በተደጋጋሚ  ጥረት ሲያደርጉ ተስተዉሏል። እንዲሁ የቆሙ ኳሶችን በማሻማት  የጭንቅላት ኳሶችንለመጠቀም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በግዙፉ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኡዶንካራ እና በአዳማ ተከላካዮች ሲመክንባቸውም ነበር። 30ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ደረጉት ሽረዎች  ከግራ መስመር የተሻማዉን ኳስ ግብ ጠባቂ መትፋቱን ተከትሎ ቢስማርክ አፒያ ወደ ግብ ቀይሮታል ።

ቀዝቃዛ በሆነበረው የሁለተኛ አጋማሽ ጨዋታ ያገኙትን አጋጣሚ በመጠቀም ረገድ የተሻሉ የነበሩት ባለሜዳዎቹ ነበሩ ። በዚሁ አጋማሽ ጎዳት የገጠመዉ ከነዓን ማርክነህ በተደጋጋሚ ወደ አሰልጣኙ ቀይረኝ የሚል ምልክት ሲያሳይ ይስተዋላል ነበር ። ተጎድቶ ጨዋታዉን የቀጠለው ከነዓን ማርክነህ 58ኛ ደቂቃ ላይ ሁለት ተጫዋቾችን ፔዳላዳ በመስራት አልፎ በግብ ጠባቂው አናት ላይ ከፍ አድርጎ ድንቅ ግብ አስቆጥሮ ለቡድኑ ይበልጥ መረጋጋትን ፈጥሯል። ከነዓን ግቡን ካስቆጠረ በኋላ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ተረጋግተዉ መጫወትን የመረጡት አዳማ ከተማዎች የተሻላ የመስመር የማጥቃት እንቅስቃሴዎችን አጠናክረው 71ኛዉ ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር የተገኝዉን የቅጣት ምት አዲስ ህንፃ ሲያሻማ ተቀይሮ የገባዉ ዐመለ ሚልክያስ በጭንቅላት ቢገጨዉም ኢላማዉ የጠበቀ አልነበረም። ሌላኛው በጨዋታው መሀል ሜዳዉን ተቆጣጥሮ የዋለዉ እና ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው አዲስ ህንፃ 75ኛ ደቂቃ ላይ በግራ መስመር አንድ ሁለት ተጫዉተዉ ይዘዉት የገቡትን ኳስ በረከት ደስታ ወደግብ አክርሮ ሲመታ በተካላካዮች ተጨርፎ ወደ ግብነት ተቀይሯል። በዚህም አዳማዎች የግብ ልዩነቱን በማስፋት ጨዋታዉን ይበልጥ መቆጣጠር ችለዋል።

በሽረ በኩል ከመጀመሪያው አጋማሽ ይበልጥ ቀዝቅዘዉ ነበር የገቡት። በሙከራ ደረጃ 84ኛ ደቂቃ ላይ ቢስማርክ አፒያ ያቀበለውን ኳስ ተቀይሮ የገባዉ አርዓዶም ገ/ህይወት ወደ ግብ ቢመታዉም ኢላማዉን አልጠበቀም። ጨዋታውም ሌላ ግብ ሳይቆጠርበት በአዳማ የ4-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ወጤቱን ተከትሎ አዳማ ከነማ በ26 ነጥብ ደረጃዉን ወደ 7ኛ ሲያሳድግ ስሑል ሽረ ባለበት በ15 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *