ደደቢት ከአዲስ ፈራሚው ጋር ተለያየ

ባለፈው ወር መጨረሻ ደደቢትን በድጋሚ በመቀላቀል ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ቆይታ ያደረገው ኢኳቶርያል ጊንያዊው የመስመር አማካይ ሮበን ኦባማ ከስራ ፍቃድ ጋር በተያያዘ ባለበት ውዝፍ ዕዳ ምክንያት ክለቡን ለመልቀቅ ተገዷል።

ባለፈው ዓመት ከደደቢት ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በኢትዮጵያ ያለውን የስራ ፍቃዱ በይፋ ሳያዘጋ ወደ ሃገሩ ያመራው ይህ ተጫዋች በድጋሚ ለደደቢት ፊርማው ቢያኖርም ላለፈው አንድ ዓመት የተወዘፈውን ዕዳ መክፈል ባለመቻሉ የስራ ፍቃዱን በመነጠቁ ነው ክለቡን መልቀቅ የቻለው።

በሃገሩ ክለብ አትሌቲኮ ማላቦ፣ ፓንተርስ እና አትሌቲኮ ሴሙ የተጫወተውና በ2012 የሃገሩ ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የተሸለመው ይህ ተጫዋች በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመመለስ ፍላጎቱ ባለመሳካቱ በትላንትናው ዕለት ወደ ሃገሩ መመለሱን ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *