ባህር ዳር ከተማ ሁለት ተጨዋቾችን አስፈርሟል

ባሳለፍነው ሳምንት ከሁለት ተጫዋቾቹ ጋር የተለያየው ባህር ዳር ከተማ በምትኩ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።
ልደቱ ለማ ከቡድኑ ፈራሚዎች አንዱ ነው። የቀድሞው የለገጣፎ አጥቂ ባለፈው ዓመት ወደ ሽረ በማምራት ከቡድኑ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደገ ሲሆን ዘንድሮ በሊጉ እና ጥሎ ማለፉ 5 ጎሎች በማስቆጠር የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነበር። ሆኖም የመጀመርያው ዙር ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ከሳምንታት በኋላ ጉዞውን ወደ ባህር ዳር ከተማ አድርጓል። ልደቱ በአጥቂ ስፍራ ላይ ቡድኑን የለቀቀው አህመድ ቢን ዋታራን ቦታ እንደሚሸፍንም ይጠበቃል።

ሚካኤል ዳኛቸው ሌላው የቡድኑ ፈራሚ ነው። የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ባህር ዳር ከተማ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና አውስኮድ የተጫወተ ሲሆን ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለሱን ተከትሎ ከቡድኑ የተሰናበተው ታዲዮስ ወልዴን ቦታ ይሰፍናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *