”ለፋሲል እንሩጥ ” የገቢ ማሰባሰቢያ ሩጫ ዛሬ ተካሂዷል

“ለፋሲል እንሩጥ” በሚል መርህ በደጋፊዎች ማኅበር የተዘጋጀዉ የገቢ ማሰባሰብያ ታላቁ ሩጫ ዛሬ ከ 6000 እስከ 6500 የሚገመቱ የዐፄዎቹ ደጋፊዎች ተሳትፈውበት በጎንደር ከተማ ተከናውኗል።

ጎንደር ከተማ ከነበረው ወቅታዊ ሁኔታ እና የመሮጫ ማልያ ሽያጭ የታሰባውን ያህል ገቢ ባለማስገኝቱ በተደጋጋሚ ለማራዘም የተገደደው ይህ ሩጫ በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ታካሂዷል። ከጠዋቱ 2:00 ላይ የህፃናቶች ሩጫ ተካሂዶ ከ1-10 ለወጡ ህፃናት የቦርሳዎች ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በአዋቂዎች ቀድመው ሩጫውን ለጨረሱ 1000 ሜዳልያዎች በሽልማትነት ተበርክቶላቸዋል።

ከዛሬው ውድድር የሚገኝውን 70 በመቶ ገቢ ለቡድኑ እንደሚያስረክብ የቀረውን 30 በመቶ ደግሞ ለሰራተኛ ደሞዝ እና ለስራ ማስኬጃ እንደሚውል ከቅናት በፊት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ የገቢ ማሰባሰቢያዎችን ያደረጉት የዐፄዎቹ የደጋፊዎች ማኅበር ከዛሬው ታላቁ ሩጫ በተጨማሪ የንግድ ትርዒት እና የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅተዉ እንደነበር ይታወሳል ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *