የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ዩጋንዳ አምርቷል

ቶኪዮ በ2020 ለምታስተናግደው የኦሊምፒክ ውድድር ለማለፍ የመጀመርያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ትላንት በአዲስ አበባ ስታድየም ከዩጋንዳ ጋር አድርገው 3-2 ያሸነፉት ሉሲዎቹ ለመልሱ ጨዋታ ዛሬ ጠዋት ወደ ካምፓላ በረዋል።

በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሶፊያ አልማሙን የተመራው የልዑካን ቡድን 28 አባላት የያዘ ሲሆን 20 ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሰልጣኝ ቡድን፣ የህክምና እና የህዝብ ግንኙነት በመያዝ ማለዳ 2:30 ላይ በረራውን አከናውኗል።

ጨዋታው ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2011 ካምፓላ በሚገኘው ፊሊፕ ኦሞንዲ ስታድየም ከቀኑ 10:00 ሲከናወን ኢትዮጵያ የ3-2 ድሏን አስጠብቃ ወደ ተከታዩ ዙር ካለፈች በቀጣይ ካሜሩንን ትገጥማለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡