ስሑል ሽረ እና ኢትዮ ፉትቦል ሶልሽን አብረው ለመስራት ተስማሙ

ስሑል ሽረዎች ኢትዮ ፉትቦል ሶልሽን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ውል በትላንትናው ዕለት ተፈራርመዋል።

በሁለተኛው ዙር ከሚገኙበት ወራጅ ቀጠና ለመላቀቅ በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች በእግር ኳስ ዙርያ ቀረፃ እና የጨዋታ ትንተና ከሚሰራው ሀገር በቀል ድርጅት ኢትዮ ፉትቦል ሶሉሽን ጋር አብሮ ለመስራት ከስምምነት ደርሷል። አራት አንቀፆች ባጠቃለለው የሁለቱ አካላት ስምምነት ኢትዮ ፉትቦል ሶሉሽን በቀጣይ በሚደረጉት ስድስት የስሑል ሽረ የሜዳ ውጭ ጨዋታዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ለመስጠት ተስማምቷል።

ተቋሙ ከወራት በፊትም ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለብ ጋር ተመሳሳይ አብሮ ለመስራት መስማማቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡