የአሰልጣኝ አስተያየት | ፋሲል ከነማ 1-1 ደቡብ ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ ከ ደቡብ ፖሊስ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ. በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች እንደሚከተለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።


ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው እንደተመለከታችሁት ቡዙ በውጥረት ውስጥ ነው የተጫወትነው። አስራ አንዱም ተጫዋቾች ሳይረጋጉ ነበር የተጫወቱት። ከዛም ግብ አስቆጠርን፤ ከዛ አልፎ አልፎ የሚመጡ የመልሶ ማጥቃት ኳሶች አስቸጋሪ ነበሩ። እኛም የተከላካይ ክፍላችንን ወደ 4 አሳድገን ብንጫዎትም መቆጣጠር አልቻልንም፤ ግብ ተቆጠረብን። ከዛ በኋላም ብዙ የማግባት እድሎች ነበሩ ግን አልተጠቀምንባቸውም። ዛሬ ለኛ ጥሩ ቀን አልነበረም።

ስለ ዳኝነቱ

ስለ ዳኝነቱ ምንም ማለት አልፈልግም። ከዳኝነቱ ይልቅ እኛ ብዙ እድሎችን አምክነናል። በእግርኳስ እንደዚህ መጥፎ ቀኖች ያጋጥማሉ። 20 ጨዋታ አድርገናል። አንድ አንድ መጥፎ ቀኖች አይጠፉም። በርግጥ በሜዳችን ነጥብ መጣላችን የሚያስቆጭ ነው። ተጫዋቾቸ ላይ አለመረጋጋት እያየሁ ነው። እሱ ላይ ለመስራት እሞክራለሁ።

ገብረክርስቶስ ቢራራ – ደቡብ ፖሊስ

እኛ ይዘን የመጣነው ሁለት አማራጮች ነው። ብንችል በመልሶ ማጥቃት አሸንፈን ለመሄድ ካልሆነ ግን አንድ ነጥብ ይዘን ለመሄድ። ምክንያቱም አንድ ነጥብ ስናገኝ ደረጃችን እንደሚሻሻል ስለምናውቅ  ሰለዚህ ባቀድነው እቅድ መሰረት ጥሩ ተጫውተና በዚህ መሰረት ያገኘነው ውጤት ጥሩ ነው ። ፋሲል በሜዳውም ከሜዳውም ውጭ ጠንካራ ነው ስለዚህ ይሄን ቡድን አንዴት ነው የምናቆመው የሚለውን እና ያ ደግሞ ሰምሮልናል።.


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡