ትውልደ ኢትዮጵያዊው በአውስትራሊያ የመጀመርያ ግቡን አስቆጠረ

በዚህ ዓመት መጀመርያ ወደ ግሪን ጉልይ ዋና ቡድን ያደገውና ከኢትዮጵያን ቤተሰቦች የተወለደው አዲሱ ባየው የመጀመርያ ጎሉን አስቆጠረ።

በአውስትራልያው ሁለተኛው የሊግ እርከን የሚወዳደረው ግሪን ጉልይ ትላንት ከሜዳው ውጭ ኪንግስተን ሲቲን አራት ለባዶ ሲረመርም አዲሱ በ57ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ባለፉት ዓመታት የታዳጊ ቡድን ቆይታው በርካታ ግቦች በማስቆጠር የሚታወቀው አዲሱ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኮከብ በመባል ዴቪዝ ሆግባን የተሰኘውን ሽልማት ከዚህ ቀደም ተሸልሟል።

በዚህ ክለብ ውስጥ ከአዲሱ ባየው ሌላ ዜና ቡጋሊ የተባለ ተስፈኛ ተጫዋች ለሃያ ዓመት በታች ቡድኑ እየተጫወተ ይገኛል።

ግሪን ጉልይ እግር ኳስ ክለብ በአውስትራልያ ሁለተኛው የሊግ እርከን ከሚገኙ ስድስት ንዑስ ሊጎች አንዱ በሆነውን ናሽናል ፕሪምየርሊግ ቪክቶርያ የሚሳተፍ ሲሆን 64 ዓመት ያስቆጠረ አንጋፋ ቡድን ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡