የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ነገ አይካሄድም

በ 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ላይ ዛሬ  ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ በጨዋታው በፊት በተነሳ ረብሻ ምክንያት ላልተወሰነ ግዜ ተራዝሟል።

ሊጀምር 40 ደቂቃዎች ያክል ሲቀረው ከስታዲየም ውጭ እና በስታዲየሙ ውስጥ በተፈጠረ ግርግር እና ሁከት ምክንያት ይጀመራል የተባለው ጨዋታ ሳይደረግ ቀርቷል። ጨዋታው በሰዓቱ እንዲደረግ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ቢያዙም ጠንከር እያለ የመጣው ችግሩ ጨዋታውን ለማድረግ አዳጋች በመሆኑ ለነገ (ዕሁድ) 3:00 እንዲደረግ ተወስኖ ነበር። ሆኖም የወላይታ ድቻ ክለብ አባላት ከተማዋን ለቀው ወደ ሶዶ በማቅናት ለእግርኳስ ፌድሬሽኑም ለድህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለፅ ጨዋታው በገለልተኛ ሜዳ እንዲደረግላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል።

የወላይታ ድቻ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በቀጣይ ፌዴሬሽኑ በሚያወጣው ቀን እና ቦታ መሠረት እንዲደረግ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ ከሁለቱ ክለቦች እና ከፌዴሬሽኑ አጣርታ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡