የሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ተራዘመ

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው ዕለት ከሚካሄዱ ጨዋታዎች አንዱ የነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር ተወስኗል።

ለጨዋታው መራዘም እንደምክንያትነት የተጠቀሰው የፀጥታ ስጋት ሲሆን የከተማው የፀጥታ አካል ኃላፊነት እንደማይወስድ መግለፁም ታውቋል። የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ከተከናወነ በኋላም ወደ ሌላ ጊዜ እንዲራዘም በመወሰኑ እንግዳው ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተማውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ተነግሯል።

በትላንትናው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታም በከተማው እና ከጨዋታው በፊት በስታዲየም በተከሰተ ነውጥ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡