የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 2-1 አዳማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው አዳማ ከተማን ካሸነፈ በኋላ አሰልጣኞቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“በተቻለን አቅም ያለውን ልዩነት ጠብቆ ለመሄድ ጥረት እናደርጋለን ” ገብረመድኅን ኃይሌ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። የመጀመርያው አጋማሽ በጥሩ ተደራጅተን ለመሄድ ሞክረን ነበር። ለማጥቃት ባደረግነው ጥረትም ግብ ማግባት ችለናል። ሆኖም በኃላ በሚያሳዝን መንገድ ግልፅ ከጨዋታ ውጭ የነበረ ኳስ በምን መንገድ ጎል እንደሆነ አልገባኝም። በዚ ሁኔታ እንዴት መቀጠል እንዳለብንም አላውቅም። እንደዚ ዓይነት ስህተት ወደማይሆን ነገር ነው የሚከትህ። ከዛ ውጭ ግን ጥሩ ነው፤ በሜዳችን አሸንፈናል። ቀጣይ ላሉብን ጨዋታዎችም ትልቅ መነሳሳት ይፈጥርልናል።

በወጥነት ስለመቀጠል

ጠንክረን እንሰራለን። ሁሉም ቡድን ከብደዋል። ሁለተኛው ዙር ከባድ ነው። ነገር ግን በተቻለን አቅም ያለውን ልዩነት ጠብቆ ለመሄድ ጥረት እናደርጋለን።

የቡድኑ የግብ ማግባት ድርሻ በተወሰኑ ተጫዋቾች ጥገኛ ስለመሆኑ

ባሉን ተጫዋቾች ነው መስራት የምንችለው። አንዳንድ ጊዜ የተገኙ የግብ ዕድሎች ያለመጠቀም አለ። ባህርዳር ላይም ተመሳሳይ ችግር ታይቶብን ነበር። በጎንደርም በተመሳሳይ ነበር። ግብ የማግባት ፍላጎትህ በጨመረ ቁጥር እንዲህ ሊያጋጥም ይችላል። ማውሊ ያጋጥመውም ተመሳሳይ ነው።

“ሱይሌማን በሁለተኛ ቢጫ መውጣቱ አግባብ አይደለም” አስቻለው ኃይለሚካኤል

ለህዝቡ ጥሩ ኳስ አሳይተናል። ያገኝናቸው ዕድሎች ያለመጠቀም ነበር፤ በኳስ ቁጥጥር ግን ተሽለን ነው የታየነው። በጎዶሎ መጫወታችን ለሽንፈታችን አስተዋፅኦ አድርጓል። በጎዶሎ ነው የተጫወትነው፤ በዛላይ የህዝቡም ተፅዕኖ አለ። ሱሌይማን በሁለተኛ ቢጫ መውጣቱ ግን አግባብ አደለም።

የዳኛው ውሳኔ ላይ ያላቸው አስተያየት

ዳኛው ለውሳኔ ፈጠነ። ከዛ በተረፈ ዳኝነቱ ጥሩ ነው። ለማስወጣት ግን ፈጥኗል።

ወሳኝ ተጫዋቾች አለመሰለፋቸው በውጤቱ ላይ የነበረው ተፅዕኖ

ያው ባለህ ተጫዋች የምትጠቀመው። ጉዳት ነው፤ ጉዳት እስከሆነ ድረስ የግድ ቡድኑ ውስጥ ያሉት ተጫዋቾችን አዘጋጅተህ ለውድድር ዝግጁ መሆን አለብህ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡