ወላይታ ድቻ የፎርፌ አሸናፊ ሆኗል


በ24ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ  ዛሬ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ የደደቢትን በሜዳ ያለመገኘቱን ተከትሎ የፎርፌ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ደደቢቶች ከፋይናንስ አቅም ጋር በተያያዘ ከ24ኛው ሳምንት በኋላ ጨዋታ ለማድረግ እንደሚቸገሩ መግለፃቸውን ተከትሎ ተከትሎ ወደ ሶዶ ያላመራ ሲሆን የዛሬው ጨዋታም በህጉ መሠረት ተፈፃሚ ሆኗል፡፡ ዛሬ ማለዳ 4:00 ላይ በቅድመ ጨወታ ስብሰባ ላይ ወላይታ ድቻ ብቻ የተገኘ ሲሆን ከሰዓት ጨዋታው በሚደረግበት ስታዲየምም አለመገኘቱን ሶከር ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝታ መመልከት ችላለች፡፡ አንድ ክለብ በሰዓቱ በሜዳ ላይ ካልተገኘ በሜዳ ላይ ለተገኘው ክለብ የጨዋታው ሙሉ ሶስት ነጥብ እና ሶስት ጎል የሚያገኝ በመሆኑ የእለቱ ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ በሜዳ ላይ ለተገኘውን ለባለሜዳው ወላይታ ድቻ 30 ደቂቃዎችን ከጠበቁ በኃላ ከረዳቶቻቸው ጋር በመሆን ህጉን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ በርካታ ደጋፊዎች ጨዋታው ባይደረግም በስታዲየሙ መታደም ችለዋል፡፡

ወላይታ ድቻ ጨዋታው ቢደረግ ይህን አሰላለፍ ይዞ ለመግባት ተዘጋጅቶ ነበር

1 መኳንንት አሸናፊ

21 እሸቱ መና – 11 ደጉ ደበበ (አ) – 23 ውብሸት ዓለማየሁ – 29 ሄኖክ አርፊጮ

24 ሃይማኖት ወርቁ – 20 በረከት ወልዴ – 8 አብዱልሰመድ ዓሊ

22 ፀጋዬ አበራ – 10 ባዬ ገዛኸኝ – 25 ቸርነት ጉግሳ

የፎርፌ ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ነጥቡን 27 ሲያደርስ ደደቢት ከ25ኛው ሳምንት ጀምሮ በድጋሚ የገንዘብ ድጋፍን በማግኘቱ ወደ ሊጉ ተሳታፊነት እንደሚመለስ አስታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡