የቡና እና መቐለ ጨዋታ ቀን ተቆረጠለት

ከሣምንት በላይ ሲያወዛግብ የቆየው ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70እንደርታ ጨዋታ ሳይካሄድ ከቀረ በኋላ መቼ ፣ የት እና በምን ሁኔታ ይደረግ የሚለው ጉዳይ ዕልባት ሳያገኝ መቅረቱ ይታወቃል። ሆኖም በጁፒተር ሆቴል በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ መግለጫ ጨዋታው ዓርብ ሰኔ 07 ቀን 2011 በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲከናወን መወሰኑን ተገልጿል።

ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከተውን የመግለጫውን ዝርዝር በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: Content is protected !!