የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከኢትዮጵያ ቡና ተለያያየ

ኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በማውጣት በ2011 የውድድር ዘመን ካስፈረመው ተጫዋቹ ጋር የኮንትራት ዘመኑ ሳይጠናቀቅ አስቀድሞ በስምምነት ተለያይቷል።

ኢትዮጵያ ቡና አማካይ ስፍራ ላይ የነበረበትን ክፍተት ለመቅረፍ በማሰብ ጋናዊው አማካይ አልሀሰን ካሉሻን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፍተኛ የሆነ የውል ማፍረሻ ገንዘብ በመክፈል ወደ ክለቡ ያስመጣው። ሆኖም አማካዩ ወጥ የሆነ አቋም ባለማሳየቱና እንደታሰበው ሆኖ ባለመገኘቱ ቀሪ አንድ ዓመት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያቆየው የውል ዘመን እየቀረው በስምምነት ሊለያዩ የቻሉት።

በሌላ ዜና ኢትዮጵያ ቡና ለ2012 የውድድር ዘመን በርከት ያሉ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ ለማስመጣት ከአንዳንድ ተጫዋቾች ጋር ድርድር የጀመረ ሲሆን በቅርቡ ዝርዝር መረጃዎችን የምናቀርብ መሆናችንን ከወዲሁ እንጠቁማለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: Content is protected !!