አፍሪካ | ኢትዮጵያ ለቀጣይ አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቋት አራት ተደለደለች

ካፍ ካሜሩን ለምታዘጀው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ቀጣይ ማክሰኞ ጁላይ 18 ከሚያካሂደው የምድብ ድልድል ቀደም ብሎ የሃገራትን ቋት ይፋ አድርጓል።

የፊፋ ወቅታዊ ደረጃን መሠረት አድርጎ በተከናከወነው የቋት (Pot) ድልድል ሃገራችን ኢትዮጵያ በቋት አራት ከብሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ፣ ሌሴቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ቦትስዋና እና ኮሞሮስ ጋር ተደልድላለች።

ለውድድሩ የሚያልፉ 23 ሀገራት የሚለዩበት የማጣርያ ውድድር 12 ምድቦች የሚኖሩት ሲሆን እያንዳንዱ ምድብ አራት ሀገራትን ይይዛል።

ቋት 1፡ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ፣ ናይጀርያ፣ ሞሮኮ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ጋና፣ ካሜሩን (አዘጋጅ ሃገር)፣ ግብፅ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ አይቮሪኮስት፣ አልጀርያ

ቋት 2፡ ጊኒ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬፕ ቨርድ፣ ዩጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ቤኒን፣ ጋቦን፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ማውሪታንያ፣ ኒጀር፣ ኬንያ፣ ሊቢያ

ቋት 3፡ ማዳጋስካር፣ ዚምባብዌ፣ ሴንትራል አፍሪካ ሪፐ.፣ ናሚብያ፣ ሴራልዮን፣ ሞዛምቢክ፣ ጊኒ ቢሳው፣ አንጎላ፣ ማላዊ፣ ቶጎ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ

ቋት 4፡ ብሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ፣ እስዋቲኒ፣ ሌሶቶ፣ ቦትስዋና፣ ኮሞሮስ፣ ኢትዮጵያ እና ከቋት አምስት የሚያልፉ አራት ቡድኖች

ቋት 5: ላይቤርያ፣ ማውሪሸስ፣ ጋምብያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቻድ፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ፣ ሲሸልስ፣ ጅቡቲ

ኤርትራ እና ሱማልያ ከቋት ድልድል ውጭ ሆነዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: Content is protected !!