የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

ወደ አንደኛ ሊግ የሚያድጉ ስምንት ቡድኖችን ለመለየት በአዳማ ከተማ ከሐምሌ 14-ነሐሴ 4 ድረስ በ36 ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የ2011 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ውድድር ነገ ይጀምራል። የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓቱም ዛሬ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የተሳታፊ ክለቦች ተወካዮች በተገኙበት ከምሽቱ 11:00 ላይ በአዳማ ከተማ ቀበሌ 12 የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት አስቀድሞ በውድድሩ አጠቃላይ ደንብ ዙርያ ውይይት ተካሂዷል። ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ከተሰጠ በኃላም በስምንት ምድብ የተከፈለ የዕጣ ድልድል ተካሂዷል።

ምድብ 1፡ ሰመራ ሎጊያ፣ ኩርሙክ ከተማ፣ ሐውዜን ከተማ፣ ሞጣ ከተማ፣ ሐረር ቡና

ምድብ 2፡ ባንቢስ ከተማ፣ ሐረር ዩናይትድ፣ ሲልቫ ስፖርት፣ ዳውሮ አላላ፣ ፍራሆም ከተማ

ምድብ 3፡ ሀሰሳ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ የኛ አዲስ ከቴ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ድሬዳዋ 04

ምድብ 4፡ መንጊ ቤኒሻንጉል፣ ደጋን ከተማ፣ ዓድዋ ውሃ አገልግሎት፣ መኩይ፣ አሚር ኑር

ምድብ 5፡ አሳይታ ከተማ፣ ኤጀሬ፣ አቃቂ ማዞርያ፣ አባድር

ምድብ 6፡ አኳ ድሬ፣ ጀኮ ከተማ፣ ሐረር ሶፊ፣ ሾኔ ከተማ

ምድብ 7፡ ካማሺ ከተማ፣ ዶዶላ ከተማ፣ መከላከያ ቢ፣ ምዕራብ አብያ

ምድብ 8፡ ድሬዳዋ 02፣ ዳጋ ዳሞት፣ ኮረም ከተማ፣ አዲስ ሱሉልታ

* በዚህ ውድድር ከየምድባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን የሚያጠናቅቁት አስራ ስድስቱ ቡድኖች በሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አሸናፊ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ አንደኛ ሊግ የሚያድጉ ይሆናል።

የመክፈቻ ጨዋታዎች


እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2011

03:00 | ሐረር ቡና ከ ኩርሙክ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

03:00
| ድሬዳዋ 04 ከ ቦዲቲ ከተማ (04 ሜዳ)

05:00
| ሞጣ ከተማ ከ ሐውዜን ከተማ (አበበ ቢቂላ)

05:00
| ሸዋሮቢት ከ የኛ አዲስ ከቴ (04 ሜዳ)

07:00
| ፍራኦል ከተማ ከ ሐረር ዮናይትድ ( አበበ ቢቂላ)

07:00
| አሚን ኑር ከ ደጋጋ ከተማ (04 ሜዳ)

09:00
| ዳውሮ አላላ ከ ሲልቫ (አበበ ቢቂላ)

09:00
| መኩይ ከ ዓደዋ ውሃ አገልግሎት (04 ሜዳ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡