ቻን 2020 | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዳማ ልምምዱን ቀጥሏል

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2020 ቻን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከጅቡቲ ጋር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዳማ ዝግጅቱን ቀጥሏል፡፡

በአዳማ ኤክስኪውቲቭ ሆቴል በማረፍ ከማክሰኞ ጀምሮ በቀን ሁለቴ በጂም እና ሜዳ ላይ ዝግጅቱን እያደረገ በሚገኘው ቡድን ሙጂብ ቃሲም በፓስፖርት ጉዳይ ምክንያት ከስብስቡ ውጪ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አቡበከር ናስር እንዲሁም ልምምድ አቋርጠው የወጡት አህመድ ረሺድ እና ግብ ጠባቂው ምንተስኖት አሎ በጉዳት የዛሬው መርሀ ግብር አካል ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡


ከማክሰኞ ጀምሮ ከቡድኑ ጋር ሲሰሩ የነበሩት አምሳሉ ጥላሁን፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ያሬድ ባዬ ደግሞ ነገ በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ቢሾፍቱ ላይ ከሀዋሳ ለሚገናኘው ፋሲል ከነማ ለመጫወት ወደ ወደ ክለባቸው አምርተዋል፡፡


በተያያዘም አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የአዳማ ከተማው ወጣቱ አማካይ ፍአድ ፈረጃን ጥሪ አድርገውለት ዛሬ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲሰራ ተመልክተነዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡