ስሑል ሽረ፣ ወልዋሎ እና መቐለ 70 እንደርታ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ዱባይ ሊያመሩ ነው

– በጉዞው ዙርያ በመጪው ሰኞ በመቐለ መግለጫ ይሰጣል

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ስሑል ሽረ ወጪያቸው በአንድ ባለሐብት አማካኝነት ተሸፍኖ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው ዱባይ ለማድረግ ዝግጅታቸው እያጠናቀቁ ይገኛሉ።

በዱባይ ቆይታቸው ከቅድመ ውድድር ዝግጅት በተጨማሪ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉት እነዚ ክለቦች በዚ ሰዓት የጉዞ እና ተያያዥ ቅድመ ሁኔታዎች እያጠናቀቁ ይገኛሉ። ሆኖም የቅድመ ውድድር ዝግጅቱ መቼ እንደሚጀመር ገና ያልተገለፀ ሲሆን ስለ ዝግጅቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ዙርያ በመጪው ሰኞ በመቐለ ኖብል ሐውስ ሆቴል መግለጫ ይሰጣል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡