ካታር 2022| ለሌሶቶው ጨዋታ ዝግጅት 27 ተጫዋቾች ተጠርተዋል


በ2022 ካታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በቅድመ ማጣርያው ከሌሶቶ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ 29 እና ጳጉሜ 3 ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ከደረሳቸው መካከል በኖርዌይ የሚጫወቱት አሚን አስካር እና ዳንኤል ተሰማ እንዲሁም በጀርመን እየተጫወተ የሚገኘው ካሊድ ሙሉጌታ ጥሪ እንደደረሳቸው ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

ሙሉ ዝርዝሩ የሚከተለውን ይመስላል

ግብ ጠባቂዎች፡ ጀማል ጣሰው (ፋሲል ከነማ)፣ ምንተስኖት አሎ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ለዓለም ብርሀኑ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዳንኤል ንጉሴ (ስትሮምጎድሴት/ኖርዌይ)

ተከላካዮች፡ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ረመዳን የሱፍ (ስሑል ሽረ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ደስታ ደሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ካሊድ ሙሉጌታ (ከክለብ ነፃ)

አማካዮች፡ ዮናስ በርታ (ደቡብ ፖሊስ)፣ ጋቶች ፓኖም (ከክለብ ነፃ)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ከነዓን ማርክነህ (ሆራያ/ጊኒ)፣ ሐይደር ሸረፋ (መቐለ 70 እንደርታ)፣ ሽመልስ በቀለ (ምስር ኤል ማቃሳ/ግብፅ)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ ቢኒያም በላይ (ስሪያንስካ/ስዊድን)፣ አሚን አስካር (ሳርፕስበርግ/ኖርዌይ)

አጥቂዎች፡ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ 70 እንደርታ)፣ ዑመድ ኡኩሪ (ስሞሀ/ግብፅ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡