ሰርዮቪች ሚሉቲን “ሚቾ” ወደ ግብፅ…


ትላንት ከኦርላንዶ ፓያሬትስ የለቀቁት አሰልጣኝ ሰርዮቪች ሚሉቲን “ሚቾ” የዛማሌክ አዲስ አሰልጣኝ ሆነው እንደተሾሙ የክለቡ ፕሬዝዳንት ገለፁ።

በአወዛጋቢ አስተያየታቸው እና አስገራሚ ውሳኔዎቻቸው የሚታወቁት የዛማሌኩ ፕሬዝዳንት ሙርታዳ መንሱር ካሊድ ጋላልን ካሰናበቱ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥረናል ብለው ተናግረው ሳምንት ሳይሞላቸው ሰርቢያዊው አሰልጣኝን መቅጠራቸውን መሕዋር ቴሌቭዥን ለተባለ የሃገራቸው ጣቢያ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከሁለት ቀን በፊት ዛማሌክ ቱዴይ ከተባለ የሬድዮ ፕሮግራም ባደረጉት ቆይታ አሌክሳንደር ስታኖዮቪችን አዲስ አሰልጣኝ አድርገው መቅጠራቸው ተናግረው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቀድሞውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደቀጠሩ ገልፀዋል። “አሌክሳንደር ስታንዮቪችን አልቀጠርነውም። እንደቀጠርን አድርጌ የተናገርኩት ሆን ብዬ ነው። ጠላታችንን ለመለየት የተጠቀምኩት ዘዴ ነው።” ሲሉም ምክንያታቸውን ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡