መከላከያዎች ተጫዋች ማስፈረማቸውን ቀጥለዋል

አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሰባት ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቁት መከላከያዎች ዛሬ ደግሞ የተከላካይ መስመር ተጫዋችን አስፈርመዋል።

ተከላካዩ አዲስ ተስፋዬ ከመከላከያ ጋር መለያየቱን ተከትሎ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የአዲስን ሁነኛ ተተኪ ሲፋላልጉ ቆይተው በመጨረሻም የቀድሞ ተጫዋቻቸው አንተነህ ተስፋዬን ለሁለት ዓመት አስፈርመዋል።

አርባ ምንጭ ከተማ በ2004 ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው አንተነህ በማስከተል ከሲዳማ ቡና እና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ወጥ የሆነ ጥሩ ብቃቱን በማሳየት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም መጫወት ችሏል። ተጫዋቹ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር አብሮ ለመቆየት ከስምምነት ደርሶ የነበረ ቢሆንም የመጨረሻ ማረፊያውን ግን መከላከያ አድርጓል።

አንተነህ በሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ድንቅ የመከላከል ጥምረት ፈጥሮ ከነበረው አበበ ጥላሁን ጋር በመከላከያ የሚገናኝ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ