ከፍተኛ ሊግ | ነገሌ አርሲ የአሰልጣኝ ቅጥር ፈፀመ

በ2011 የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ለተጋጣሚ ቡድን በሜዳው ፈተኝ የነበረው ነገሌ አርሲ አሰልጣኝ ታዬ ናኒቻን ለመቅጠር ተስማምቷል።

ባለፈው የውድድር ዘመን የአንደኛ ሊጉ ዱከም ከተማን ሲመሩ የነበሩት አሰልጣኙ በታዳጊዎች ላይ ለረጅም ጊዜያት የሰሩ ሲሆን በተጨማሪም በኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ክፍል ኃላፊነት እንዲሁም በሰበታ ከተማ በአሰልጣኝነት እና በስራ አስኪያጅነት ሰርተው አልፈዋል።

ነገሌ አርሲ ከሁለገቡ ባለሙያ ታዬ ናኒቻ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ እንደሚያደርግ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ