ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የአሰልጣኝ ቅጥርን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ መጥራቱን አስታውቋል።

ክለቡ ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በሸራተን አዲስ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ የቀጣይ አሰልጣኝ ቅጥር ጉዳይ ላይ ማብራርያ እንደሚሰጥ ሲጠበቅ በመግለጫው ላይ አዲሱ አሰልጣኝ ማንነት ይፋ ስለመሆኑ እና የፊርማ ስነሥርዓት ስለመኖሩ ግን በክለቡ ጥሪ ላይ አልተገለፀም።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓመቱ መጀመርያ ፖርቱጋላዊው ቫዝ ፒንቶን አሰናብቶ ስቴዋርት ሀልን ቢሾምም እንግሊዛዊው አሰልጣኝም ከወራት ቆይታ በኋላ ተሰናብተው በምክትል አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ መሪነት የውድድር ዘመኑን ማገባደዱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: