ከፍተኛ ሊግ | የአዲስ አበባ ከተማ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽኑ አሰምተዋል

በ2011 በአዲስ አበባ ክለብ ውስጥ የውል ኮንትራት እያላቸው ደመወዝ ያልተከፈላቸው የቡድኑ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ቡድኑን አስተዳደር ብንጠይቅም ምላሽ አልተሰጠነም በሚል ለፌዴሬሽኑ አቤቱታን አቅርበዋል፡፡

ተጫዋቾቹ “የቡድኑ አስተዳደሮች ለማግኘት ብዙ ጊዜ ጥረናል። ሁሉም ተጨዋቾች የቤተሰብ ኃላፊነት ያለብንን በመሆኑ የደሞዝ አልከፈለንም። እስከ አሁን በተደጋጋሚ ክለቡ ክፍያን እንዲፈፅም ብንጠይቅም ተግባራዊ ሊያደርግ አልቻለም። ስለዚህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በገባነው ውል መሠረት ተፈፃሚ ያድርግን” ሲሉ ቅሬታቸውን በደብዳቤ ገልጸዋል፡፡

ደብዳቤው ይህን ይመስላል


© ሶከር ኢትዮጵያ