የ2012 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በዛሬው ዕለት አዲስ በገዛው ህንፃ ላይ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ ምስረታን አስመልክቶ በተዘጋጀው መግለጫ ላይ በአዲሱ የሊግ ፎርማት ዙርያ አዳዲስ መረጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በመግለጫው ላይ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው በሚያካሂዱት ሊግ ቻምፒዮኑ የሚለይበት የሚለይበት መንገድ የተገለፀ ሲሆን የየምድቡ አሸናፊ የሆኑ ሁለት ቡድኖች በገለልተኛ ሜዳ በሁለት ዙር የፍፃሜ ጨዋታ አድርገው አሸናፊው ቡድን ዋንጫውን የሚያነሳ ይሆናል። አሸናፊው ቡድን ኢትዮጵያን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሚወክል ሲሆን ሁለተኛ በመሆን የሚያጠናቅቀው ቡድን ደግሞ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል፡፡ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊውየ የሚሆነው ቡድን ኢትዮጵያን በሴካፋ ውድድር የሚካፈል ይሆናል፡፡

በተያያዘም ሊጉ በምድብ መከፈሉን ተከትሎ የሚፈጠረው የጨዋታ ቁጥር መቀነስን ለመቅረፍ አዲስ ሦስተኛ የውድድር ፎርማት ስለመጀመር መታቀዱ ተገልጿል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ