ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች | ወደ ፍፃሜ የደረሱ ቡድኖች ታውቀዋል

በዕለተ ረቡዕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን ያስተናገደው የሴካፋ ዋንጫ የፍፃሜ ተጋጣሚዎችን ሲለይ ኤርትራውያን ተጫዋቾች ጠፍተዋል።

ከሳምንት በፊት በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የጀመረው እና በርካታ ግቦች እያስተናገደ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች እያስመዘገበ በግማሽ ፍፃሜ የደረሰው የሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች ዋንጫ ትላንት ሲቀጥል ታንዛንያ እና ኬንያ በፍፃሜው አገናኝቷል። ኬንያ ኤርትራን 1-0 ፤ ታንዛንያ ደግሞ ሱዳንን 2-1 በማሸነፍ ወደ ፍፃሜ ገብተዋል። የፍፃሜው ጨዋታም በመጪው እሁድ በፉፋ ቴክኒካል ሴንተር (ንጁሩ) ይካሄዳል።

በሌላ ዜና አምስት የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች በዩጋንዳ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ጨዋታው ከመካሄዱ በፊት በጂንጃ ከተማ ከሚገኘው ስፓክ ሆቴል የጠፉት እነዚ ተጫዋቾች ቁጥራቸው አምስት ሲሆን ውድድሩን በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ የሚገኝው መዋዕል ተስፋይ ይገኝበታል።

ከግብ አስቆጣሪው መዋዕል ውጭ ሃኒባል ግርማይ፣ ሊበን ግብጻዊ፣ ስምዖን አስመላሽ እና ሄርሞን ፍስሃየ ሌሎች የጠፉ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ