ኢትዮጵያ ቡና ተስፋኛ ወጣት ተጫዋች አስፈረመ

በወጣት ተጫዋቾች እየተገነባ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ለወደፊት ተስፋኛ መሆኑን እያሳየ የሚገኘውን ወጣቱን አጥቂ አስፈርሟል።

በ2008 በክለብ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ከ17 ዓመት በታች ቡድንን በመቀላቀል ከዛም በመቀጠል ከ20 ዓመት በታች ቡድን እና ዘንድሮ ዋናው ቡድን ማገልገል ችሏል። ያለፉትን አራት ዓመታት በጥሩ ብቃት ያገለገለ የሚገኘው የመስመር አጥቂው አላዛር ሽመልስ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ባለ ተስዕጦው የግራ መስመር አጥቂ አላዛር ፊርማውን ማኖሩ በአዲስ አስተሳሰብ በወጣት ተጫዋችች እየተገነባ ላለው ኢትዮጵያ ቡና መልካም ዜና ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ