የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሥራ ድርሻ ላይ ሽግሽግ ተደረገ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የሥራ ድርሻ ሽግሽግ አድርጓል።

ባልተሟሉ አባላት በተደረገው በዚህ ስብሰባ ላይ በ2011 ውድድር ዓመት የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት ኮሎኔል ዐወል አብዱራሂም የእግርኳስ ልማት ኮሚቴ ሆነው ሲሾሙ የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ አዲስ በሚዋቀረው የግዢ ክፍል ዋና ኃላፊ ሆነዋል። አቶ ኢብራሂም አህመድ ከከፍተኛ ሊግ ዋና ኃላፊነት ተነስተው የዳኞች ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ሲመደቡ አቶ አሊሚራህ መሐመድ የከፍተኛ ሊግ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል። ሌሎቹ አባላት ደግሞ በነበሩበት ቦታ እንደሚሰሩ ለማወቅ ተችሏል።

በቀጣይ ፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴን ጨምሮ በተጓደሉ ቦታዎች ምትክ ምደባ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ