የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ከ20 ቀናት በኋላ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲከናወን የምድብ ድልድሉ ይፋ ተደርጓል።

ከኅዳር 4-13 ድረስ በታንዛኒያው ቻማዚ ስታዲየም የሚከናወነው በዚህ ውድድር ላይ ስምንት ሀገራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሲጠበቅ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም በዕጣ ድልድል ውስጥ ተካቷል።

ምድብ ሀ፡ ታንዛኒያ፣ ብሩንዲ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን

ምድብ ለ፡
ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ

መክፈቻ ጨዋታዎች

ሐሙስ ኅዳር 4 ቀን 2012
ብሩንዲ ከ ዛንዚባር
ታንዛኒያ ከ ደቡብ ሱዳን

ዓርብ ኅዳር 5 ቀን 2012
ኢትዮጵያ ከ ኬንያ
ዩጋንዳ ከ ጅቡቲ


© ሶከር ኢትዮጵያ