የደቡብ ሠላም ዋንጫ ዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ወደ ነገ ሲሸጋገር የመካሄዱ ነገርም አጠራጥሯል

የደቡብ ካስቴል ዋንጫ በሚል ሥያሜ ያለፉትን ዓመታት ሲደረግ የነበረው እና ወደ ደቡብ ሠላም ዋንጫ የተለወጠው ውድድር ዘንድሮ የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጥሯል፡፡

ውድድሩ ዛሬ አመሻሽ የዕጣ ማውጣት ስነስርአት ከተደረገ በኃላ ለአስር ቀናት ይካሄዳል ተብሎ መርሀ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓቱ ከዛሬ ወደ ነገ ተሸጋግሯል ተብሏል። አመሻሹን ደግሞ ውድድሩ ላይደረግ የሚችልበት ሁኔታ ሰፊ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ነገ ከፀጥታ አካላት ጋር የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውይይት አድርገው ስምምነት ላይ መድረስ ከቻሉ ሊደረግ እንደሚችል ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን ይህ ካልተሳካ ግን ላይደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል። ለውድድሩ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ ክለቦችም እንደማይደረግ በመስማታቸው ወደየመጡበት መመለስ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ