የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 2-1 ሀድያ ሆሳዕና

መቐለ 70 እንደርታ በመጀመርያው የሊጉ መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 ካሸነፈበት ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

“ካለብን የተጫዋቾች አማራጭ ችግር አንፃር ውጤቱ ጥሩ ነው” ገ/መድህን ኃይሌ

ስለ ጨዋታው

የመጀመርያ ጨዋታ እንደመሆኑ ውጤቱን እንፈልገው ነበር። ጨዋታው በዝግ መሆኑ አስቸጋሪ ነበር፤ ከዛ በተጨማሪ የአማራጭ እጥረት ነበረን። ካለብን የተጫዋቾች አማራጭ ችግር አንፃር የመጣው ውጤት ጥሩ ነው። በቀጣይ በቅጣት ያላሰለፍናቸው ተጫዋቾች ይመለሳሉ። በህመም ካጣናቸውም መሻሻል የሚያሳዩ ከሆኑ ወደ ቡድናችም እንቀላቅላለን። በአጠቃላይ ስናየው ግን እንደ ጅማሮ ጥሩ ጅማሮ ነው።

ጨዋታው በዝግ መሆኑ ስለፈጠረው ተፅዕኖ እና ከደጋፊ ጋር ከሚደረግ ጨዋታ ጋር ስላለው ልዩነት

አንደኛ ልዩነቱ ዳኝነት ላይ ነው። ደጋፊ ካለ ውሳኔዎች አወሳሰን ላይ ጥንቃቄ ይኖራል። ሌላው ደጋፊው የሚሰጥህ ሞራል መነሳሳት ይፈጥራል። በዚ ላይ ደግሞ ደጋፊያችን ትልቅ ሚና ስላለው ጨዋታው በዚህ መጠናቀቁ ጥሩ ነው።

“ውጤቱ አይገባንም፤ መቀበል ስላለብን ግን ተቀብለናል” የሆሳዕና ምክትል አሰልጣኝ ኢዘዲን ዐብደላ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። በሁለቱም ቡድኖች በኩል የታየው የመሸናነፍ ስሜት ጥሩ ነበር። ያለንን አቅም አውጥተን ለመጠቀም ሞክረናል። ውጤቱ አይገባንም። መቀበል ስላለብን ግን ተቀብለናል።

ስለ ቡድናቸው

ለሊጉ አዲስ ነን። ግን እንደ አዲስ አደለም እየተጫወትን ያለነው። ራዕያችን ረዥም ነው። ባሉን ክፍተቶች ሰርተን ተፎካካሪ ለመሆን ነው እየሰራን ያለነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ